Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dacl

Department of Aging and Community Living
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about DC Department of Aging and Community Living for Amharic speakers.

የቢሮው ስም:  የዲሲ አረጋውያን ቢሮ

ተልዕኮ:

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት አረጋውያን ቢሮ ተልዕኮ ለአረጋውያን መከራከር፣ ፕላን ማውጣት፣ በሥራ ላይ ማዋል እና የጤና፣ የትምህርት፣ የሥራ እና ከጥገኝነት የሚያላቅቅ፣ እድሜ ባለጠጋነትንና ሰብዓዊ ክብርን የሚያበረታቱና ለአረጋዊያን ምርጫ የሚመቹ የማህበራዊ አገልግሎቶት ፕሮግራሞችን መቆጣጠር ነው። 

ዋና ፕሮግራሞች:

ፕሮግራሙ የተቀረጸው ጥብቅና፣ አመራር፣ አስተዳደር፣ ፕሮግራም እና  የገንዘብ ኃላፊነቶችን ለማካሄድ ነው።  በፕሮግራም ደረጃ የአረጋውያን ቢሮ በቦታው ላይ የሚከናወኑ ሁለት ፕሮግራሞችን ማለትም የመረጃ እና እርዳታ ማዕከል እንዲሁም የአረጋዊያን ስልጠናና ቅጥር ፕሮግራሞችን ይከታተላል። በተጨማሪም የDCOA በአካል ጉዳተኝነት ዕድሜ 18 እና ከዛ በላይ ለሆናቸው የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች አገልግሎቶችን ይሰጣል።

አገልግሎቶች:

የሥራ ሥልጠና እና የቅጥር ፕሮግራም                                                                           

ዕድሚያቸው ከፍ ላለ ሠራተኞች ቅጥር እና የሥልጠና ፕሮግራም (OWETP) ዕድሜያቸው 55 እና ከዛ በላይ የሆኑ የዲስትሪክቱ ነዋሪዎችን በስልጠና ፕሮግራም እና በህዝብ/በግል ጥምረቶች የሥራ ምደባን በተመለከተ ይረዳቸዋል።

 

መረጃ እና ትብብር                                                                                             

ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ከ8፡30 ኤም እስከ 5:00 ፒኤም አረጋዉያን፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ተንከባካቢዎቻቸው እና አጠቃላይ ህብረተሰቡ ወደ አንድ አማካይ ቦታ በመደወል ለአዋቂዎች ዝግጁ የሆኑ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኙ አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ።  እንዲሁም  ወደ ቢሮ በመምጣት ሠራተኞችን ማናገር ወይም ስለሚሰጡት አገልግሎትችና ፕሮግራሞች በጽሁፍ ያሉ መረጃዎችን መውሰድ ይችላሉ። 

 

ዋን-ስቶፕ የሪሶርስ ማዕከል                                                                                                              

የአረጋውያንና የአካል ጉይዳተኝነት ሪሶርስ ማዕከል (ADRC) የዲስትሪክቱ ለአዋቂዎችና ለአካል ጉዳተኞች ዋን-ስቶፕ ሲሆን ዕድሚያቸው 60 እና ከዛ በላይ ለሆናቸው ሰዎች እና 18 እና ከዛ በላይ ዕድሜ ላላቸው አካል ጉዳተኞች መረጃዎችንና አገልግሎቶችን ይሰጣል።  መንግሥት አቀፍ እና በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት አንድ ጊዜ ብቻ ይደውሉ።

 

ተጨማሪ የምግብ ምርት ፕሮግራም (CSFP)፣ የአረጋውያን ገበሬዎች የምግብ ገበያ (SFMNP)                         

CSFP የምግብ ሸቀጦች እና የአመጋገብ ትምህርት አገልግሎቶችን 60 ዓመትና ከዛ በላይ ለሆናቸው ለአረጋውያን፣ ለነፍሰ ጡር እና አራስ ሴቶች እና ከስድስት ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ይሰጣል። SFMNP ለተጠቃሚዎች ንጹህ ፍራፍሬ እና አትክልቶችን ለመግዣ ቼኮችን ይሰጣል።

 

መሪ መሥሪያ ቤት

ስምንት መሪ የሆኑ መሥሪያ ቤቶች መጠነ ሰፊ የሆኑ ማህበራዊና የጤና አገልግሎቶችን በሁሉም የዲስትሪክቱ ስምንት ዋርዶች ይሰጣሉ።  እነኝህ መሥሪያ ቤቶች የማህበረሰቡ ሳተላይቶች በመሆን ከነባር ዋሽንግቶናውያኖች ጋር ያለንን ግንኙነቶች ያጠናክራሉ።  በተጨማሪም አስፈላጊ የሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን፣ ንጥረ ምግቦችን፣ ማማከር፣ ትምህርት፣ ኬዝ ማኔጅመንት፣ ቤትና ምግቦች፣ መረጃና ትብብር፣ የስልክ ማረጋገጫዎች፣ የጤና ማበረታቻ ፕሮግራሞች፣ መዝናኛና ማህበራዊ ግንኙነቶች ያቀርባሉ። 

 

የመሪ መሥያ ቤት አገልግሎት አካባቢዎች

ዋርድ 1:

Terrific Inc.                                                                         

910 Westminster Street NW, Washington, DC 20009

(202) 882-1160

 

ዋርድ 5:

Seabury Ward 5 Aging Services                   

2900 Newton Street, NE, DC 20017          

(202) 529-8701

 

ዋርድ 2:

Terrific Inc.          

1220 L Street N.W,  DC 20001                     

(202) 882-1160

ዋርድ 6:

Seabury Ward 6 Aging Services                                

555 Water Street SW, Washington, DC 20024

(202) 397-1725

 

ዋርድ 3:

IONA Senior Services                                

4125 Albemarle Street, NW, DC 20016   

(202) 966-1055

 

ዋርድ  7:

East River Family Strengthening Collaborative

3917 Minnesota Avenue NE, Washington, DC 20019

(202) 534-4880

 

ዋርድ 4:

Terrific Inc.                                                                      

418 Missouri Avenue, NW DC 20009      

(202) 882-1160

 

ዋርድ  8:                                                                                                                                                                                            

East River Family Strengthening Collaborative Ward 8                                                       

4301 9th St. SE, DC 20002                                                   

(202) 562-6860

 

 

የአረጋውያን የኔትዎርክ አገልግሎቶች  

DCOA 27 የሚሆኑ ኮሚኒቲ ተኮር ያለትርፍ የተቋቋሙ ድርጅቶችን (ሶስት ዩንቨርስቲዎችን ጨምሮ) 33 የአረጋውያን ፕሮግራሞችን በማቀፍ የአረጋውያን ኔትዎርክ አገልግሎትን በገንዝብ እየረዳ ያንቀሳቅሳል። አገልግሎቶቹም የአዋቂዎች መዋያ፣ የመርሳት ችግር ላለባቸው አገልግሎቶች፣ የተንከባካቢ ድጋፍ፣ የኬዝ ሜኔጅመንት፣ ማማከር፣ የድንገተኛ መጠለያ አገልግሎት፣ ሥራ የማስያዝ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የጋራ የእኩለ ቀን ምግቦች፣ የጤና ዋስትና ማማከር፣ በቤት የሚሰጡ ምግቦች፣ የቤት ውስጥ ድጋፍ፣ የህጋዊ ድጋፍ፣ ረዘም ላለ ጊዜ የሚደረግ የእንክብካቤ ድጋፍ፣ ለብዙ አላማ የሚሆኑ የአረጋውያን ማዕከሎች፣ የንጥረ ምግብ ምክር፣ የእርጅና እና የአካል ጉዳተኝነት ሪሶርስ ማዕከላት፣ መዝናኛ እና ማህበራዊ መስተጋብሮች፣ የእፎይታ እርዳታ አገልግሎቶች፣ የተለዩ ዝግጅቶች፣ መጓጓዣ እና የአካል እንቅስቃሴ ማዕከላትን ያካትታል።

 

የማስተርጎም አገልግሎቶች:

ስለ ዲሲ የአረጋውያን ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች መረጃ እና ትብብር ካስፈለገዎ በ(202) 724-5626 ይደውሉ።  ወደቢሯችን ሲመጡ ወይም ሲደውሉ አንዱ የሥራ ባልደረባችን በአካል ከሚያስተረጉም ሰው ጋር በማገናኘት ወይም በቋንቋ መስመር አማካይነት እንረዳዎታለን።

አድራሻችን:

DC Department of Aging and Community Living

500 K Street N.E.

Washington DC 20002

202-724-5626

d[email protected]